ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች ውጪ ያለ ከሃዲ ይቅርና እነርሱን ራሱ በቃልኪዳን የሚኖሩ እንኳን ቢሆኑ ለነርሱ ቀድሞ ሰላምታ ማቅረብን ከለከሉ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነርሱ መካከል አንዱን መንገድ ላይ ስናገኘው ወደ ጠባቡ መንገድ እንድናስጠጋው ገለፁ። መሃል መንገዱን ይዞ መሄድ ያለበት አማኝ ነው። ከመሃል መንገድ ዘወር የሚለው ከሃዲው ነው። በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ሙስሊም የተናነሰ መሆን የለበትም።