ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስሊሞችን ገንዘብ ያለአግባብ ስለሚጠቀሙና ያለአግባብ ስለሚበዘብዙ ሰዎች ተናገሩ። ይህም ገንዘብን ባልተፈቀደ መልኩ ማጠራቀምና ማግኘትን እንዲሁም ትክክለኛ ባልሆነ ቦታ ፈሰስ ማድረግን የሚጠቀልል ሀሳብ ነው። የየቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ ወቅፍ የተደረገን ገንዘብ መብላት፣ አደራዎችን መካድ፣ የማህበረሰቡን ገንዘብ ያለአግባብ መውሰድ ሁሉ እዚህ ውስጥ ይካተታል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የትንሳኤ ቀን የነዚህ ሰዎች ምንዳ እሳት መሆኑን ተናገሩ።