explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለቅርብ ዘመዶቹ ያለበትን ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ዝምድናውን የቆረጠ ሰው ወይም ያወካቸውና ያስከፋቸው ጀነት ላለመግባት የተገባ ነው ብለው ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ዝምድናን መቁረጥ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
  • ዝምድናን መቀጠል በተለምዶ በሚታወቀው መልኩ ነው የሚሆነው። ቦታ፣ ዘመንና ሰዎቹ እንደመለያየታቸው ይለያያል።
  • ዝምድናን መቀጠል በመዘየር፣ ሶደቃ በመስጠት፣ ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ሲታመሙ በመጠየቅ፣ በመልካም በማዘዝ፣ ከመጥፎ በመከልከልና በሌሎችም መልኩ ይፈፀማል።
  • ዝምድናው የሚቆረጠው ሰው እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆነ ቁጥር ወንጀሉም እጅግ የከፋ ይሆናል።