ዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከአንድ በዘንባባ ነገር ተሰፍቶ በተሰራ ትንሽ ምንጣፍ ላይ ተኙና ሲነሱም ሰሌኑ የጎናቸው ቆዳ ላይ ሰንበር አወጣ። እኛም እንዲህ አልን: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለርሶ ለስላሳ ፍራሽ ብናዘጋጅሎት’ኮ በዚህ ሸካራ ሰሌን ላይ ከሚተኙ ይልቅ የተሻለ ይሆንሎታል።" ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "ከዱንያ ጋር ወደርሷ እስክማረክ ድረስ የሚያደርሰኝ ውዴታ የለኝም። የኔና እርሷ ውስጥ ያለኝ ቆይታ ምሳሌ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ዛፏን ትቶ እንደሚሄድ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለም።"