ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።