ዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: ሁሉንም ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር በጽሑፍ መጠበቅ ፈልጌ እጽፈው ነበር። ከቁረይሽ የሆኑ ሰዎችም እንዲህ በማለት ከለከሉኝ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ፤ ሊሳሳቱም ይችላሉ።" እኔም ከመጻፍ ተቆጠብኩኝ። እነርሱ የተናገሩትን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገርኳቸው። በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: "ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በደስታም ይሁን በንዴት በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብሆን ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።" በርግጥ ከፍ ያለው አላህም ስለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም።* እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጂ ሌላ አይደለም።} [አንነጅም:3 -4]