ልኡካኖች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። ወደርሳቸውም የደረሱ ጊዜ እርሳቸውን ለማሞገስ ፈልገው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያልወደዷቸውን የተወሰኑ ንግግሮች ተናገሩ። "አንቱ አለቃችን የሆኑ!" አሏቸው። ነቢዩም ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የሁሉም አለቃ አላህ ነው።" በፍጡራኑ ላይ የተሟላ አለቃነት የርሱ ነው። ፍጡራን ባሮቹ ናቸው። "በደረጃ በላጫችን የሆኑ" አሉ። ማለትም በደረጃ፣ በልቅና ከፍ ያሉ ማለት ነው። "እጅግ ታላቅ የሆኑ" በጣም ለጋስ፣ ከፍታና ልቅና ያለዎት ለማለት ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተለመደውን ንግግራቸውን እንዲናገሩ፣ በቃላቶች ወሰን እንዳያልፉና ክልክል ወደሆነው ሺርክና መዳረሻዎቹ ለሚዳርገው ወሰን ማለፍና ያልተገባ ሙገሳም ሰይጣን እንዳይጎትታቸው (መጠንቀቅ እንዳለባቸው) ሱሓቦችን ጠቆሙ።