ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) በአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ የወረደውና የተላኩበት ዕድሜ አርባ መሆኑን፤ ከወሕይ መውረድ በኋላም በመካ አስራ ሶስት አመት መቆየታቸውን፤ ከዚያም ወደ መዲና እንዲሰደዱ እንደታዘዙና በመዲናም አስር አመታት እንደቆዩ፤ ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በስልሳ ሶስት አመታቸው እንዳረፉ ተናገሩ።