ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለባልደረቦቻቸው እጅግ ትልቅ ስለሆነ ወንጀል ነገሯቸው። እነዚህን ሶስት ወንጀሎችንም ጠቀሱ፦ 1 - በአላህ ማጋራት፦ ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፣ ከአላህ ውጪ የሆነን አካል ከአላህ ጋር በተመላኪነቱ ወይ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ እኩል ማድረግ ማለት ነው። 2 - የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፦ ይህም ወላጆች ላይ በንግግርም ይሁን በተግባር በማንኛውም መልኩ ማወክና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው። 3 - ውሸት መናገር ነው። በውሸት መመስከርም እዚህ ውስጥ ይካተታል: ይህም ከተቀጠፈበት አካል ንብረቱን ለመውሰድ ወይም ክብሩ ላይ ወሰን ለማለፍ ወይም የመሳሰሉትን በመፈለግ የተቀጠፈና የተዋሸ ንግግር ሁሉ ማለት ነው። ከመደጋገማቸው የተነሳ ሶሐቦች ለነቢዩ ካላቸው እዝነትና የሳቸውን መረበሽ ጠልተው ምነው ዝም ባሉ ብለው እስኪመኙ ድረስ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የውሸትን ፀያፍነት እና ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረውን መጥፎ አሻራ ለማስገንዘብ ከሐሰተኛ ቃል ደጋግመው አስጠነቀቁ።