ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶስት አይነት ሰዎችን በውርደትና ክስረት አፍንጫቸው በአፈር እንዲታሽ ረገሟቸው: የመጀመሪያው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱ ዘንድ ተወስተው በርሳቸው ላይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወይም እርሱን የመሰለ ውዳሴ በማለት በርሳቸው ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው ነው። ሁለተኛው: የረመዷንን ወር አግኝቶ ከዚያም አምልኮን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ምክንያት ከመማሩ በፊት ወሩ የተጠናቀቀበት ሰው ነው። ሶስተኛው: በእርጅና ወቅት ወላጆቹን አግኝቶ የነርሱን ሐቅ ባለመወጣቱና ሐቃቸውን በማጓደሉ ምክንያት ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑለት ሰው ነው።