ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተከታዩን ዚክር ስላለ ሰው እንዲህ ብለው ተናገሩ (ላ ኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ) በተመላኪነቱም፣ በጌትነቱም፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹም ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። (ለሁል ሙልኩ) ሁሉም ማስተዳደርና ማስተናበር የርሱ ነው። (ወለሁል ሐምድ) በሚፈጥረውና በሚወስነው ሁሉ ምስጋና የርሱ ነው። (ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) ያለምንም ከልካይ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። እርሱ ያልሻውም አይሆንም። በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ደጋግሞ ይህንን ውዳሴ ያለ ሰው ለርሱ አላህ ዘንድ አስር ባሪያዎችን ነፃ ያወጣ ሰው ምንዳ ይፃፍለታል፤ መቶ ምንዳና ጀነት ውስጥ ያለ ደረጃም ይፃፍለታል፤ መቶ ወንጀሎችም ከርሱ ላይ ይሰረዙለታል፤ ፀሐይ በመጥለቋ ምሽቱ እስኪገባ ድረስም ቀኑን ከሸይጧን ማጥመምና ቁጥጥር መከለያ፣ መጠበቂያ፣ መመሸጊያና ጋሻ ትሆንለታለች፤ የትንሳኤ ቀንም እርሱ ከሰራው አብዝቶ ያለ ሰው ካልሆነ በቀር ማንም በላጭ ስራ ይዞ አይመጣም።