በዚህ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደሚነግሩን ይህንን ውዳሴ ያለ፦ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙም: "ከአላህ ውጪ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ብቸኛና ለሱ አጋር የለውም፤ ጥራት የተገባው አላህ በምሉዕ ንግስና የተለየ ነው፤ ከሱ ውጪ ያሉት የማይገባቸውን ውዳሴና ሙገሳ ከውዴታና ልቅና ጋር በብቸኝነት የተገባው ነው ፤ እርሱም አንዳችም የማያቅተው ቻይ ነው።" ማለት ነው። ይህንን ታላቅ ውዳሴም በቀን አስር ጊዜ የደጋገመም ሰው በነርሱ ላይ የአላህ ሶላትና ሰላም ይስፈንና የኢብራሂም ልጅ ከሆኑት ከኢስማዒል ዘሮች አራት ባሮችን ከባርነት ነፃ እንዳወጣ ሰው ምንዳ አምሳያ ለርሱ ይኖረዋል። የኢስማዒል ዐለይሂ ሰላም ዘሮች የተለዩትም እነርሱ ከሌሎች የላቁ ስለሆኑ ነው።