አንዳንድ ድሃ ሶሐቦች ያሉበትን ሁኔታና ድህነታቸውን፣ ብዙ ገንዘብ ያላቸው ወንድሞቻቸው ሶደቃ በመስጠት ብዙ ምንዳ እንዳገኙት እነርሱ ግን በድህነታቸው ምክንያት ይህን ብዙ ምንዳ ለማግኘት ሶደቃ መስጠት እንዳልቻሉና እንደነርሱ ብዙ መልካም ምንዳ የሚያገኙበትን መፍትሄ ፍለጋ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስሞታ አቀረቡ፡ ሀብታሞቹ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመውም ይጾማሉ፤ ሀብታሞች በትርፍ ገንዘቦቻቸው ምፅዋት ሲሰጡ እኛ ግን ምፅዋት አንሰጥም። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሊያደርጉት የሚችሉትን ሶደቃ በመጠቆም እንዲህ አሏቸው: "በራሳቹ ላይ የምትመፀውቱትን ነገር አላህ አላደረገላችሁምን? (ሱብሓነሏህ/ ጥራት ለአላህ የተገባው ነው) በማለታችሁ ለናንተ የሶደቃ ምንዳ ያስገኝላችኋል፤ ልክ እንደዚሁ (አሏሁ አክበር/ አላህ ታላቅ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (አልሐምዱሊላህ/ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (ላኢላሃ ኢለሏህ/ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከዚህም በላይ ሚስታችሁን መገናኘታችሁ ራሱ ሶደቃ ነው።" ሶሐቦችም ተገርመው "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላስደሰተ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "ንገሩኝ እስኪ ብልቱን ዝሙት ላይ ወይም ከዛ ውጪ በሆነ ክልክል ቦታ ላይ ቢያኖራት በርሱ ላይ ወንጀለኝነት አይኖርበትምን? ልክ እንደዚሁ የሚፈቀድለት ቦታ ላይ ካኖራት ደሞ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።