ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመካ መንገድ ላይ እየተጓዙ ሳለ ጁምዳን በሚባል ተራራ ላይ ሲያልፉ እንዲህ አሉ: "ይህ ጁምዳን ነው ተጓዙ! ሙፈሪዶች ቀደሙ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሙፈሪዶች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "አላህን በብዛት የሚያወሱ ወንዶችና ሴቶች ናቸው።" አሉ።» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።