ከአልአገርሪ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።