ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት ጠየቁ ልዕለ ኃያሉ ንጉስ አላህ ዘንድ በላጩን፣ የላቀውን፣ የፋፋውን፣ የፀዳውንና የጠራውን ስራችሁን እንድነግራችሁ ትፈልጋላችሁን ጀነት ውስጥም ያለውን ደረጃችሁን ከፍ የሚያደርግላችሁን ስራስ ማወቅ ትፈልጋላችሁ? ወርቅና ብር ከመመፅወትም ለናንተ የሚበልጥላችሁን? ከከሀዲያን ጋር ለውጊያ ተገናኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትቀሉና አንገቶቻችሁንም ከሚቀሉ የሚበልጠውን ስራ ማወቅ ትፈልጋላችሁን? ሶሐቦችም: አዎ ይህንን ማወቅ እንፈልጋለን አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ወቅትና በአጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ አላህን ማውሳት ነው አሏቸው።