ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው በሚያወሩት ሐዲሥ አንድ ባሪያ አንድ ወንጀል ሰርቶ ከዚያም "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" ካለ አላህ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀሉን የሚምረው፣ የሚሸሽገውና ይቅር የሚለው ወይም በወንጀሉ የሚቀጣው ጌታ እንዳለው አወቀ! በርግጥም ምሬዋለሁ" እንደሚል ነገሩን። ከዚያም ባሪያው በድጋሚ ወንጀል ይሰራና "ጌታዬ ወንጀሌን ማረኝ!" ይላል። አላህም "ባሪያዬ ወንጀልን ሰራ። ወንጀሉን የሚምረው፣ የሚሸሽገውና ይቅር የሚለው ወይም በወንጀሉ የሚቀጣው ጌታ እንዳለው አወቀ! በርግጥም ለባሪያዬ ምሬዋለሁ" ይላል። ከዚያም ባሪያው በድጋሚ ወንጀል ይሰራና "ጌታዬ ወንጀሌን ማረኝ!" ይላል። አላህም "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀሉን የሚምረው፣ የሚሸሽገውና ይቅር የሚለው ወይም በወንጀሉ የሚቀጣው ጌታ እንዳለው አወቀ! በርግጥም ምሬዋለሁ። ወንጀልን በሰራ ቁጥር ወንጀሉን በመተውና በመፀፀት ዳግም ወደ ወንጀል ላለመመለስም ቆርጦ እየወሰነ ነገር ግን ነፍሱ እያሸነፈችው ወንጀል ላይ በድጋሚ እየወደቀ በዚህ መልኩ ወንጀል ቢሰራም ተውበት ማድረግን እስካዘወተረ ድረስ የሰራውን ቢሰራ እምረዋለሁ። ተውበት ያለፈውን ወንጀል ታብሳለችና።" ይላል።