አዛን ማለት የሶላት ወቅት መግባቱን ለሰዎች ማሳወቂያ ነው። የአዛን ቃላቶች የኢማንን መሰረተ ሀሳቦች የጠቀለሉ ቃላቶች ናቸው። በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አዛን በሚሰማ ወቅት የተደነገገውን ገለፁ። እሱም አዛን ሰሚው አዛን ባዩ እንደሚለው ማለቱ ነው። አዛን ባዩ 'አላሁ አክበር' ያለ ጊዜ ሰሚውም 'አላሁ አክበር' ይላል በዚህ መልኩ አዛን ባዩ ያለውን በማለት ይቀጥላል። 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' እና 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' በሚልበት ጊዜ ግን ሰሚው 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ' ይበል። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህን ቃላቶች ከልቡ አጥርቶ ከአዛን ባዩ ጋር የመላለሰ ሰው ጀነት እንደሚገባ ገለፁ። የአዛን ቃላቶች ትርጉም: "አላሁ አክበር" ማለት ጥራት የተገባው አላህ ከሁሉም ነገር እጅግ ታላቅና የላቀ ነው ማለት ነው። "አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ" ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ማለት ነው። "አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" ማለት ሙሐመድ አላህ የላካቸው የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውንና እሳቸውን መታዘዝም ግዴታ መሆኑን በምላሴና በልቤ እርግጠኛ ሆኜ እመሰክራለሁ ማለት ነው። "ሐይየ ዐለስ-ሶላህ" ማለት ወደ ሶላት ኑ! ማለት ሲሆን ሰሚው የሚለው "ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለት ደግሞ የአላህን ትእዛዝ ለመተግበር ከሚከለክሉ ነገሮች ለመዳን የሚያስችል ብልሀትም፤ ለመተግበር የሚያስችል ሀይልም፤ በማንኛውም ነገር ላይም ችሎታ የለም በአላህ መግጠም ቢሆን እንጂ ማለት ነው። "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ማለት ወደ ስኬት መንገድ ኑ! ማለት ነው። ስኬቱም ጀነትን ማግኘትና ከእሳት መዳን ነው።