ሙዓዊያ ቢን አቡ ሱፍያን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መስጂድ ውስጥ ክብ ወደሰሩ ሰዎች መጡና ለምን ጉዳይ እንደተሰበሰቡ ጠየቃቸው። እነርሱም "አላህን እያወሳን ነው።" አሉ። ሙዓዊያም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በመቀመጣቸውና በመሰብሰባቸው አላህን ከማውሳት በቀር ሌላን እንዳልፈለጉ አስማሏቸው። እነርሱም ማሉላቸው። ቀጥሎ "በእውነተኝነታችሁ ላይ ጠርጥሬያችሁ አይደለም ያስማልኳችሁ።" አሏቸው። ቀጥሎም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እንደርሱ ቅርብ የነበረና የርሱ ቅርበት እህቱ ኡሙ ሐቢባም የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሚስት ስለነበረችና እርሱም ወሕይ ፀጸሐፊ ስለነበረ ነው። ከመሆኑም ጋር ግን ጥቂት ሐዲስ ያስተላለፈው እርሱ እንደነበር ተናገረ። አንድ ቀን ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከቤታቸው እንደወጡና መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው አላህን እያወሱ፤ አላህ ለእስልምና ስለመራቸውና እስልምናን ስለለገሳቸውም እያመሰግኑት አግኝተዋቸው ልክ ሙዓዊያ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ባልደረቦቹን እንዳስማላቸው ሁሉ ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠይቀው እንዳስማሏቸው ተናገረ። ቀጥሎም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነርሱን የጠየቁበትንና ያስማሉበትን ምክንያት ተናገሩ። እርሱም መልዐኩ ጂብሪል የአላህ ሰላም በርሱ ላይ ይስፈንና እርሳቸው ጋር መጥቶ አላህ በናንተ መላእክቱን እንደሚፎካከር የናንተንም ደረጃ ለነርሱ እንደሚገልፅ፣ የስራችሁን ውበት እንደሚያሳያቸውና እነርሱ ዘንድም በናንተ ላይ እንደሚያወድስ ነገረኝ አሉ።