ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የርሳቸውን ሐዲሥ ሰምቶ ለሌላው እስኪያደርስ ድረስ የሸመደደ ሰው አላህ በዱንያ ውስጥ ውበትን፣ ቁንጅናና ብርሃንን እንዲሰጠው፤ በመጪው አለም ደግሞ ወደ ጀነት ብርሃን፣ ፀጋና ውበት አላህ እንዲያደርሰው ዱዓ አድጉለት። አንዳንዴ ሐዲሥ የሚነገረው ሰው ሐዲሡን መጀመርያ ከሰማው ሰው የበለጠ ሸምዳጅ፣ ተገንዛቢ፣ ከሐዲሡ ፍሬሃሳቦችን መዞ የሚያወጣ ይሆናል። በዚህም የመጀመሪያው ሰውዬ በአስተማማኝ መልኩ መሸምደዱንና "ነቅል" (መውሰድን) ሲችል ሁለተኛው ደግሞ በአስተማማኝ መልኩ መገንዘቡንና መረዳቱን የቻለ ይሆናል።