ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የቂያማን መቅረብ ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል የሸሪዐ ዕውቀት መነሳቱን ገለፁ። ይህም የሚሆነው ዑለሞች በመሞታቸው ነው። የዚህም ውጤት የመሀይምነት መሰራጨትና መብዛትን፣ የፀያፍ ድርጊቶችና ዝሙት መስፋፋትን፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት መብዛትን ያስከትላል። ለሀምሳ ሴቶች ጉዳይ የሚያስፈፅመውና የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማሟላት ኃላፊነት የሚወስደው አንድ ወንድ እስኪሆን ድረስ የወንዶች ቁጥር ሲመነምን የሴቶች ቁጥር ደግሞ ይጨምራል።