አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ሃይማኖቱን መገንዘብ እንደሚቸረው፤ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ከሰጣቸው ሲሳይ፣ ዕውቀትና ሌሎችም ነገሮች የሚያከፋፍሉና የሚያሰራጩ አከፋፋይ ብቻ እንጂ ትክክለኛው ሰጪ አላህ ብቻ እንደሆነ ከሱ ውጪ ያሉት ከሰበብነት የዘለለ ከርሱ ፈቃድ ውጪ እንደማይጠቅሙ፤ ይህ ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ ከመቆም እንደማይወገድና ትንሳኤ እስከሚቆም ድረስም የተፃረራቸው እንደማይጎዳቸው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።