ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ባሪያ የሞተ ጊዜ የቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ጀነት ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ የሚገኘውን ልዩ ማረፊያውና ስፍራው ይቀርብለታል። የጀነት ነዋሪ ከሆነ የጀነት ስፍራው፤ የእሳት ነዋሪ ከሆነም የእሳት ስፍራው ይቀርብለታል። እንዲህም ይባላል: "ይህ የትንሳኤ ቀን የምትቀሰቀስበት ማረፊያህ ነው።" ይህም ለአማኞች ማስደሰቻ ሲሆን ለከሃዲያን ደሞ መቀጣጫ የሆነ ንግግር ነው።