ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና አንድ የቁርኣን ምእራፍ እንደሚያስተምሩት ትኩረቱን ወደርሳቸው ለመሰብሰብ እጁን በእጃቸው ውስጥ አድርገው ሶላት ውስጥ የሚባለውን ተሸሁድ አስተማሩት። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለተሸሁድ በቃል ደረጃም ይሁን በመልዕክት ደረጃ የሰጡትን ትኩረት የሚጠቁም ነው። እንዲህም አሉ: "አትተሒይያቱ ሊላህ… " ይህ ማለት: ክብርና ልቅናን የሚጠቁም ንግግርም ይሁን ተግባር ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው ማለት ነው። "… አስሶለዋቱ… " ይህም ማለት የታወቁት ግዴታ ሶላቶችም ይሁኑ ሱና ሶላቶች ለአላህ ናቸው ነው። "… አጥጦይዪባቱ… " ይህም ማለት: ምሉዕነትን የሚጠቁሙ ጥሩ ንግግሮች፣ ተግባሮችና ባህሪያቶች ሁሉ ለአላህ የተገቡ ናቸው ማለት ነው። "… አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ… " "አንቱ ነቢይ ሆይ! ሰላም፣ የአላህ እዝነትና በረከቱ በርሶ ላይ ይሁን" ይህም ለርሳቸው ከሁሉም መከራና ጉዳት ሰላም እንዲሆኑና ሁሉም መልካም ነገሮች እንዲጨምርላቸውና እንዲበዛላቸው የምናደርገው ዱዓእ ነው። "… አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን… " (በአላህ ደጋግ ባሮችና በኛ ላይም ሰላም ይስፈን።) ይህም በሰማይ ውስጥም ሆነ በምድር ውስጥ ለሚገኝ ደግ ባሪያና ለሰጋጁ ሁሉ ሰላም እንዲሰፍንበት የሚደረግ ዱዓእ ነው። … አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ… " "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ቁርጥ የሆነ ማረጋገጥን አረጋግጣለሁ ማለት ነው። "… ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" "ሙሐመድ የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።" ማለትም: ለርሳቸው በባርነትና በመጨረሻ መልዕክተኛነት አረጋግጣለሁ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰጋጁ የፈለገውን ዱዓእ እንዲመርጥ አነሳሱ።