ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶላታቸው ውስጥ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሙስሊም የሆነ ሰው በእጅጉ የሚፈልጋቸው ጉዳዮችንና የዱንያንም ሆነ የአኺራን መልካም የሰበሰቡ የሆኑትን: ምህረትን፤ የወንጀል መሸሸግን፤ ይቅር መባልን መፈለግ፤ እዝነቱ እንዲያዳርሰው መፈለግ ፤ ከሚያምታታ፣ ዝንባሌው ከሚገፋፋውና ከበሽታዎችም ጤናማ መሆንን መፈለግ ፤ አላህን ለእውነትና በርሱ ላይ በመፅናት ላይ እንዲመራው መጠየቅ፤ የኢማን፣ የእውቀት ፣ የመልካም ስራ፣ ምርጥና ሐላል የገንዘብ ሲሳይ እንዲለግሰው መለመንን ሁሉ ያጠቃለሉ የሆኑትን እነዚህ አምስት ዱዓዎችን ይለምኑ ነበር።