ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። አላህን ያመሰገነ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ ምስጋናውን ተቀብሎ ይመነዳዋል ማለት ነው። ከዚያም "አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" በሚለው ንግግራቸው ሰማያትን፣ ምድሮችን፣ በመካከላቸው ያለውን፣ አላህ የሻውን ነገርንም ሁሉ በሚሞላ ምስጋና አላህን ያመሰግኑ ነበር።