ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። እኔም የአላህ መልክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁንሎና በተክቢራ እና በፋቲሓ መካከል ዝምታዎን አይቻለሁና ምንድን ነው የሚሉት? አልኳቸው። እርሳቸውም " 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ አልላሁምመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዱ ሚነድደነስ፣ አልላሁምመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ' ነው የምለው" አሉኝ። (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው በኔና በወንጀሌ መካከል አራርቅ! አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፉ እንደሚጠራው እኔንም ከወንጀሎቼ አጥራኝ! አላህ ሆይ በጤዛ፣ በውሃና በበረዶ ከወንጀሎቼ እጠበኝ። ማለት ነው።)» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ፋቲሓ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። በዚህ ዝም ባሉበት ወቅትም ሶላታቸውን በአንዳንድ ዱዓ ይከፍታሉ። ከነዚህ ከተላለፉልን ዱዓዎች መካከልም: "አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ አልላሁመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዱ ሚነደነስ፣ አልላሁመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ።" ሰውዬው በዚህ ዱዓ በምስራቅና ምዕራብ መካከል ፈፅሞ መገናኘት እንደማይኖረው ሁሉ ከርሱ ጋር በማይገናኙ መልኩ በርሱና በወንጀሎቹ መካከልም አላህ ዐዘ ወጀል እንዲያራርቅ እና ወንጀል ላይ እንዳይወድቅ፤ ወንጀል ላይ ከወደቀ እንኳ ነጭ ልብስ ከእድፍ እንደሚጠራው ከወንጀሉ እንዲያጠራውና እንዲያስወግድለት፣ ከወንጀሉ እንዲያጥበውና የወንጀሉን ሀሩርና ወላፈንንም በውሃ፣ በጤዛና በረዶ እንዲያቀዘቅዝለት ነው ዱዓ የሚያደርገው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሶላቱ ጮክ ተብሎ የሚቀራበት ቢሆን እንኳ ዱዓንና የሶላት መክፈቻን ዝግ አድርጎ ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በእንቅስቃሴም ይሁን እርጋታ ላይ ያላቸውን ሁኔታ ለማወቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንረዳለን።
  • ሌሎችም የመክፈቻ ዱዓዎች መጥተዋል። በላጩ ሰውዬው ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመጡትንና የፀኑትን የመክፈቻ ዱዓዎች በመከተልና በመሸምደድ አንዳንዴ ይሄንን አንዳንዴ ደግሞ ሌሎቹን እየቀያየረ ቢል ነው።