ሶሐቦች አትተሒያቱ ላይ "አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀ ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ… " በማለት በነቢዩ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደሚቀርብ ካወቁ በኋላ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ ሶላት እንዴት እንደሚደረግ ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ እንዴት ሶላት እንደሚያወርዱ ነገሯቸው። ትርጉሙም: "አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመድ" ማለትም: አላህ ሆይ! በላይኛው አለም፤ በርሳቸው፣ እምነታቸውን በተከተሉና አማኝ በሆኑ ቅርብ ዘመዶቻቸውም ላይ በመልካም ትውስታ አወድሳቸው። "ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂም" በኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) የአላህ ሰላም ይስፈንባቸውና ቤተሰቦች ‐ እነሱም ኢብራሂም፣ ኢስማዒል፣ ኢስሐቅ፣ ዝርያዎቻቸውና አማኝ ተከታዮቻቸው ‐ ላይ ችሮታህን እንደዋልከው በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይም ችሮታህን ዋል። "ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ" ማለትም: በዛትህ፣ በባህሪትህ እና በድርጊቶችህ ምስጉን የሆንክ፤ በልቅናህ፣ በስልጣንህና በስጦታህ ሰፊ የሆንክ አንተው ነህ ማለት ነው። "አልላሁመ ባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ መሐመድ ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂም" ማለትም ለነቢዩ ከመልካሙና ከክብር የላቀውን ስጣቸው፣ ጨምርላቸውም፣ አፅናላቸውም።