ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገራቸው የማይከስርበትንና የማይፀፀትበትን ዚክር ተናገሩ። እንደውም በቃላቶቹ ምንዳ የሚያገኝባቸው ናቸው። ከፊሉ ከከፊሉ በኋላ የሚባሉ ሲሆኑ ከግዴታ ሶላት በኋላ ነው የሚባሉት። እነርሱም: "ሱብሐነላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት። ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው። "አልሐምዱሊላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት ነው። ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ነው። "አላሁ አክበር"ን ሰላሳ አራት ጊዜ ማለት ነው። አላህ ከሁሉም ነገር ታላቅና የላቀ ነውና።