ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውጫዊ ንፅህና በውዱ እና በገላ ትጥበት የሚተገበር እንደሆነና የሰላት ቅድመ መስፈርት እንደሆነም ይነግሩናል ። "አልሐምዱሊላህ ሚዛንን ትሞላለች " የሚለው ነቢያዊ ንግግር :- ጥራት ይገባውና አላህን ማወደስ እንዲሁም ምሉዕ በሆኑ ባህሪያቶች እሱን መግለፅ፥ የትንሳኤ ቀን ስትመዘን የስራዎችን ሚዛን ትሞላለች ማለት ነው። "ሱብሐነላህ ወልሐምዱሊላህ " የሚለውን መናገር አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራትና እሱን ከመውደድና ማላቅ ጋር ለግርማው የሚመጥን በሆነ የተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ሲሆን በሰማያትና ምድር መሀል ያለውንም ይሞላል። "ሰላት ብርሃን ነው። " ለአንድ ሰው ለቀልቡም፣ ለፊቱም ፣ በቀብሩም ውስጥ ፣ በትንሳኤ ቀንም ብርሃን ይሆንለታል። "ምፅዋት ማስረጃ ነው።" ምፅዋት የአንድ አማኝ ኢማን እውነተኝነትንና ለምፅዋት የተገባውን ቃልኪዳን ባለማመኑ ምፅዋት ከመስጠት ከሚታቀበው ሙናፊቅ ተቃራኒ መሆኑንም የሚጠቁም ማስረጃ ነው። "ትእግስት (አንፀባራቂ ብርሃን) ወገግታ ነው።" ትእግስት ማለት ነፍስን ከትእግስት ማጣትና መበሳጨት መቆጣጠር ሲሆን ትእግስት እንደ ፀሀይ ብርሀን ሀሩርና ማቃጠል አብሮት የሚኖር ብርሃን ነው። ምክንያቱም መታገስ ነፍስን መታገልና ከዝንባሌዋ ማቀብ የሚፈልግ ስለሆነ አስቸጋሪ ነው። ታጋሽ ሰው ብርሃናማ፣ የተመራና በትክክለኛነት ላይ ዘውታሪ ከመሆን አይወገድም። ትእግስት ሲባል አላህን በመታዘዝ ላይ ፣ አላህን ከመወንጀል በመራቅ ላይ መታገስ እና ከመከራና ከአለማዊ የችግር ዓይነቶች መታገስ ነው። ቁርኣንን በማንበብና ተግባራዊ በማድረግህ ምክንያት "ቁርኣን ላንተ ማስረጃ ነው።" ወይም በሱ ሳይሰሩና ሳያነቡ ቁርኣንን በመተዉ ምክንያት "በአንተ ላይ ማስረጃ ይሆናል።" ቀጥሎ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች ሁሉ እንደሚለፉ፣ ለተለያዩ ተግባራትም እንደሚበታተኑ፣ ከእንቅልፋቸው በመንቃት ለተለያዩ ተግባራት ከቤቶቻቸው እንደሚወጡ ተናገሩ። ከነሱም መካከል በአላህ ትእዛዝ ላይ በመፅናት ነፍሱን ከእሳት ነፃ የሚያወጣ ሲኖር ፤ ከነሱም ውስጥ ከዚህ የአላህ ትእዛዝ በመዘንበል ወንጀል ውስጥ የሚወድቅና ነፍሱ እሳት ውስጥ በመግባቷ ለጥፋት የሚዳርጋት አለ።