ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤት በሚገባ ወቅትና ምግብ ከመመገባችን በፊት አላህን ማውሳት አዘዙ። እርሱ ቤት በሚገባ ወቅትና ምግቡን በሚጀምር ወቅት አላህን (ቢስሚላህ) በማለት ያወሳ ጊዜ ሰይጣን ለግብረ አበሮቹ "እዚህ ባለቤቱ አላህን በማውሳት ከናንተ የተጠበቀበት በሆነው ቤት ውስጥ ምንም ማደሪያም እራትም የላችሁም።" ይላቸዋል። ሰውዬው ቤቱ በሚገባ ወቅትና ምግብ በሚመገብበት ወቅት አላህን ካላወሳ ግን ሰይጣን ለግብረአበሮቹ እዚህ ቤት ውስጥ ማደሪያም እራትም እንዳገኙ ይነግራቸዋል።