የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተናገረችው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} የሚለው ምዕራፍ የወረደላቸው ጊዜ ቁርአኑን ወደ ተግባር ለመለወጥ {ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው! ምህረትንም ለምነው።} የሚለውን የአላህን ትእዛዝ ፈጥነው ለመፈፀም በሶላት መሀል በሩኩዓቸውና በሱጁዳቸው ወቅት እንዲህ ማለትን ያበዙ ነበር፡ "ሱብሓነከ" ለአንተ ከማይመጥን ከሁሉም ጉድለት አንተን አጠራኸለሁ። "አልላሁምመ ረበና ወቢሐምዲክ" ዛትህ፣ ባህሪህና ድርጊትህ ምሉዕ ስለሆነ ምስጉን በሆኑ ውዳሴዎች አወድስሃለሁ። "አልላሁምመግፊርሊ" ከኔ ላይ ወንጀሌን አብስ! ይቅር በለኝ።