ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ "አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ" ይሉ ነበር። ቀጥለውም ጌታቸውን "አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) በማለት ጌታቸውን ያልቃሉ። አላህ በባህሪያቶቹ የተሟላና ሰላም ነው፤ ከሁሉም ጉድለትና ነውርም የጠራ ነው። ከዱንያና አኺራ ክፋት ሰላም የሚፈለገውም ከሌላ ሳይሆን ከርሱ ነው። እርሱ ጥራት ይገባውና በሁለቱም ዓለም መልካሙ የበዛ ፣ የልቅናና መልካም ባለቤት ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከሶላት በኋላ ኢስቲግፋር ማለትና በርሱ ላይ መዘውተር እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • አምልኮ ውስጥ የጎደለውን እንዲሞላ፣ አምልኮ ውስጥ ያሳነስነውን እንዲጠግን ኢስቲግፋር እንደሚወደድ እንረዳለን።
explain-icon

ተጨማሪ