የተወሰኑ ሰዎች ወደ አንድ ሶሐባ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር ሲያደርጉ የሚጠቀሙበት ሚንበር ከምን እንደተሰራ ሊጠይቁት መጡ። በዚህ ዙሪያም አየተነታረኩና እየተከራከሩ ነበር። ሱሓቢዩም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አናጢ አገልጋይ ወደነበራት የአንሷር ሴት "ለሰዎች ንግግር በማደርግበት ወቅት የምቀመጥበትን ሚንበር ለኔ እንዲሰራልኝ አገልጋይሽን እዘዢልኝ።" በማለት መልዕክተኛ መላካቸውን፤ እርሷም ትእዛዛቸውን በመቀበል አገልጋዩዋን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጦርፋእ ዛፍ ሚንበር እንዲሰራ ማዘዟን፤ ያጠናቀቀ ጊዜም ሚንበሩን ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መላኳን እርሳቸውም መስጂድ ውስጥ ቦታው ላይ እንዲቀመጥ አዘው መቀመጡንና ሚንበሩ ላይም መስገዳቸውን አወሳ። ሚንበሩ ላይ ሆነው ተክቢራ አደረጉ፣ እርሱ ላይ እንዳሉም ሩኩዕ አደረጉ፣ ከዚያም ፊታቸውን ወደኋላ አቅጣጫ ሳያዞሩ ወደኋላ እያፈገፈጉ በመውረድ ሚንበሩ ስር ሱጁድ ወረዱ፣ ከዚያም ወደ ሚንበሩ ተመለሱ። በዚህ መልኩ ሰግደው እንዳጠናቀቁም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት እንድትከተሉኙና አሰጋገዴን እንድታውቁ ነው።"