ሶሐቢዩ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሶላትን አሰገዱ። ተሸሁድ በሚባልበት ስፍራ ላይ የደረሱ ጊዜም ከኋላቸው ከሚሰግዱ ሰጋጆች መካከል አንዱ "ቁርአን ውስጥ ሶላት ከበጎነትና ዘካ ጋር ተቆራኘች።" አለ። አቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሶላቱን ባጠናቀቁ ጊዜ ወደ ተከታዮቹ በመዞር "ከመካከላችሁ 'ቁርአን ውስጥ ሶላት ከበጎነትና ዘካ ጋር ተቆራኘች።' ብሎ የተናገረው ማን ነው?" በማለት ጠየቋቸው። ሰዎቹም ዝም አሉ። ከነርሱ ውስጥ ማንም አልተናገረም። ጥያቄያቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ደገሙት። አቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የሚመልስላቸው ያጡ ጊዜ ደፋርነቱን ስለሚያውቁ፣ ከርሳቸው ጋር ቅርርብና ትስስር ስላለው መጠርጠሩ በማያስከፋው መልኩ ትክክለኛውን ተናጋሪ ለማጋለጥ "ሒጧን ሆይ! አንተ ነህ መሰለኝ ያልከው?" አሉ። ሒጧንም አለመናገሩን በመግለፅ ከራሱ ላይ ለመከላከል እንዲህ አለ: "እኔም የተናገርኩ መስሎህ ትወቅሰኛለህ ብዬ ፈርቼ ነበር።" በዚህ ወቅት ከሰዎቹ መካከል አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ነኝ ያልኩት መልካምን አስቤ እንጂ አልተናገርኩም።" አቡ ሙሳም እሱን እያወገዙ ለማስተማር እንዲህ አሉ: "ሶላታችሁ ውስጥ ምን እንደምትሉ አታውቁምን?" ቀጥለውም አቡ ሙሳ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ጊዜ ኹጥባ እንዳደረጉላቸውና ሸሪዓውን እንዳብራሩላቸው፣ ሶላታቸውንም እንዳስተማሯቸው ተናገሩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የሰገዳችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ፣ ቀጥ በሉ ከዚያም ከመካከላቸው አንዱ ሰዎችን ይምራ። ኢማሙ የመክፈቻ ተክቢራ ያለ ጊዜ እንደርሱ አምሳያ ተክቢራ አድርጉ፤ ፋቲሐን የቀራ ጊዜና {غَيرِ المَغضوبِ عَلَيهِم وَلَا الضّالّينَ} [አልፋቲሐ:7] የሚለው ጋር የደረሰ ጊዜ አሚን በሉ ይህንን ከፈፀማችሁ አላህ ዱዓችሁን ይቀበላችኋልና፤ ኢማሙ ተክቢራ አድርጎ ሩኩዕ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጋችሁ ሩኩዕ አድርጉ። ኢማሙ ከናንተ በፊት ሩኩዕ ያደርጋል ከናንተ በፊትም ቀና ይላልና እንዳትቀድሙት። ኢማሙ ወደ ሩኩዕ ሲወርድ የቀደማችሁ ቅፅበት እናንተ ኢማሙ ቀና በሚልበት ቅፅበት ወቅት ሩኩዕ ላይ በመዘግየታችሁ ይካካሳል። ያቺ ቅፅበት በዚህች ቅፅበት ትካካሳለች። በዚህ የናንተም የሩኩዕ ቆይታ እንደርሱ የሩኩዕ ቆይታ ይሆናል። ኢማሙ 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' ያለ ጊዜ 'አላሁመ ረበና ለከል ሐምድ' በሉ። ሰጋጆች ይህንን ያሉ ጊዜ አላህ ዱዓቸውንና ንግግራቸውን ይሰማቸዋል። ምክንያቱም የጠራውና ከፍያለው አላህ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' 'አላህ ያመሰገነውን ሰሚ ነው' ብሏልና። ቀጥሎ ኢማሙ ተክቢራ አድርጎ ሱጁድ የወረደ ጊዜ ተከታዮቹም ተክቢራ አድርገው ሱጁድ መውረድ ይገባቸዋል። ኢማሙ ሱጁድ የሚወርደውም ሆነ የሚነሳው ከነርሱ በፊት ነውና። ያቺ ቅፅበት በዚህች ቅፅበት ትካካሳለች። የተከታዩ (የመእሙሙ) የሱጁድ መጠን እንደ ኢማሙ የሱጁድ መጠን ይሆናል። ለተሸሁድ የተቀመጠ ጊዜ የሰጋጅ የመጀመሪያ ቃሉ እንዲህ ማለት ይሁን: 'አትተሒይያቱ፣ አጥጦይዪባቱ፣ አስሶለዋቱ ሊላሂ'፤ 'ንግስና፣ ዘውታሪነትና ልቅና ሁሉ እንዲሁም አምስቱ ሶላቶችም ለአላህ የተገቡ ናቸው።' 'አስሰለሰሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ አስሰላሙ ዐለይና ወዐላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን' ከሁሉም ነውር፣ መከራ፣ ጉድለትና ብልሽት ሰላም እንዲያደርጋችሁ አላህን ተማፀኑ። ነቢያችንን ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰላምታ ለብቻ እንነጥላቸዋለን። ከዚያም ከአላህ ሀቆችና ከባሮቹ ሀቆች ያለባቸው ግዴታዎችን በተወጡ የአላህ ደጋግ ባሪያዎች ላይም ሰላም እንዲሰፍን ዱዐ እናደርጋለን። ከዚያም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልዕክተኛው እንደሆኑ እንመሰክራለን።"