ከዋኢል ቢን ሑጅር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ሰገድኩኝ። ወደ ቀኛቸው "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ" በማለት ያሰላምቱ ነበር። ወደ ግራቸው ዞረው ደሞ "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ" ይሉ ነበር።» ሐሰን ነው። - አቡዳውድ ዘግበውታል።