ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በስርቆት እጅግ በጣም መጥፎ ሰው ከሶላቱ የሚሰርቅ ሰው መሆኑን ገለፁ። ይህም ከዚህ ሌባ ተቃራኒ የሰውን ገንዘብ የወሰደ በዚህች አለም ሊጠቀምበት ይችል ይሆናል። ይህ ሌባ ግን ከራሱ የምንዳና አጅር ሐቅ የሚሰርቅ ነው። ሶሐቦችም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንዴት አንድ ሰው ከሶላቱ ይሰርቃል?" ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም "ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን አያሟላም።" ብለው መለሱ። ይህም በሩኩዑም በሱጁዱም ሲጣደፍ በተሟላ መልኩ እነርሱን አለመፈፀሙ ነው።