ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ በሶስት ስፍራዎች በትከሻቸው ትይዩ እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። የመጀመሪያው ወቅት: የመክፈቻ ተክቢራ ወቅት ሶላትን የጀመሩ ጊዜ ነው። ሁለተኛው: ለሩኩዕ ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ነው። ሶስተኛው: ጭንቅላታቸውን ከሩኩዕ ቀና ያደረጉና "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ ረበና ወለከል ሐምድ" ያሉ ጊዜ ነው። ሱጁድ ማድረግ በሚጀምሩበት ወቅትም ሆነ ከሱጁድ በሚነሱበት ወቅት ግን እጃቸውን ከፍ አያደርጉም ነበር።