የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያለው: የተውሒድን ቃል ትርጉሙን አውቆ የሚያስፈርደውንም በመስራት የተናገረ ሰው፤ እንዲሁም በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባርነትና መልክተኝነት የመሰከረ፤ የዒሳን ባርነትና መልክተኝነት ያመነ፤ አላህ ዒሳን "ሁን" በሚለው ቃሉ እንደፈጠራቸውና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ ነፍስ እንደሆኑም የመሰከረ፤ አይሁዶች ወደርሷ ካስጠጉት ዘለፋም እናቱን መርየምን ያጠራ፤ መኖራቸውንና የአላህ ፀጋና ቅጣቱ መሆናቸውን ከማመን ጋር ጀነትም እውነት መሆኑን፣ እሳትም እውነት መሆናቸውን ያመነ ሰው በአምልኮዎች ላይ ያጓደለና ወንጀሎችም ያሉበት ቢሆን እንኳ በዚህ እምነት ላይ ከሞተ መመለሻው ወደ ጀነት ነው።