አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን በነፍሱ ውስጥ የሚመላለስ ነገርን በውስጡ ይሰማዋል። ነገር ግን እሱን ከመናገር ይልቅ አመድ መሆን እስኪመኝ ድረስ እሱን መናገር ይከብደዋል። መልክተኛውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁለት ጊዜ ተክቢር በማሰማት የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ ብቻ በመመለሱ አላህን አመሰገኑ።