የተወሰኑ የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች ወደርሳቸው በመምጣት አስቀያሚና እጅግ የሚፀየፉት በመሆኑ ሳቢያ ለመናገር የሚከብዳቸው የሆነ ነገር በነፍሳቸው ውስጥ ስለሚከሰት ትልቅ ጉዳይ ጠየቋቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ይህ በውስጣችሁ የተሰማችሁ ነገር ግልፅ ኢማንና ሰይጣን በልባችሁ የሚጥለውን ለመከላከል የሚያነሳሳችሁ እንዲሁም በነፍሶቻችሁ ውስጥ እሱን መናገር እንድታወግዙና እንዲከብዳችሁ የሚያደርግ የእምነት እርግጠኝነት ነው። ሰይጣን ልቦችችሁን አልተቆጣጠረምና ነው። ሰይጣን ልቡን የተቆጣጠረው ግን ውስጡ የሚሰማውን እንዳይናገረው የሚከለክለውን አያገኝም።" በማለት መለሱላቸው።