ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢማን ተግባሮችን፣ እምነቶችንና ንግግሮችን የጠቀለለ ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ተናገሩ። ከኢማን ክፍሎች ውስጥ በላጩና ከፍተኛው ትርጉሙን አውቆ ፣ የሚያስፈርደውን በመተግበር "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው። አላህ አንድና ብቸኛ አምላክ መሆኑንና ለአምልኮ የተገባ ብቸኛ አምላክ መሆኑን ከርሱ ውጪ ያለ ማንም አምልኮ እንደማይገባውም ማመን ነው። የኢማን ትንሹ ስራ ሰዎችን የሚያውክ የሆነን ነገር ሁሉ ከመንገዳቸው ላይ ማስወገድ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሓያእ (አይነ አፋርነት) የኢማን አንድ ክፍል መሆኑን ተናገሩ። ይህም መልካም ለመስራትና ፀያፍ ለመተው የሚያነሳሳ ባህሪ ነው።