ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢማኑ ላይ እውነተኛ አማኝ የሆነና ልቡ በኢማን የተረጋጋ ሰው እነዚህን ሶስት ነገሮች ከወደደ ልቡ ውስጥ መስፋት፣ መደሰት፣ ማጣጣም እንደሚሰማውና ወደ አላህ የመቅረብን እርካታ እንደሚያገኝ ተናገሩ። የመጀመሪያው: በአላህ ጌትነት መውደድ ነው። ይህም በርሱ ላይ የአላህን ጌትነቱን የሚያስፈርዱ ሲሳይ ማከፋፈልና ሁኔታዎችን መወሰን ሲከሰትበት ልቡ ውስጥ አንዳችም ተቃውሞ አያገኝምም፤ ከአላህ ውጪ ጌታንም አይፈልግም። ሁለተኛ: በእስልምና ሃይማኖት መውደድ ነው። ይህም እስልምና ላካተታቸው ሀላፊነቶችና ግዴታዎች ልቡን መክፈቱና ከእስልምና መንገድ ውጪ ላለ ሃይማኖት ልቡን አለመክፈቱ ነው። ሶስተኛ: በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መልክተኝነት መውደድ ነው። ይህም እርሳቸው ይዘውት ላመጡት ነገር ባጠቃላይ ምንም ሳይጠራጠርና ሳያወላውል ልቡን መክፈትና መደሰት፤ የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ የገጠመውን ካልሆነ በቀር ላያደርግ ነው።