ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።" ሶሒሕ ነው። - ሓኪምና ጦበራኒይ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አዲስ ልብስን ለረጅም ጊዜ በመገልገላችን ምክንያት እንደሚደክም ሁሉ ኢማንም በሙስሊም ቀልብ ውስጥ እንደሚደክምና እንደሚያረጅ ተናገሩ። ይህም አምልኮ መፈፀምን በማቋረጥ ወይም ወንጀልን በመፈፀምና በስሜት ውስጥ በመዘፈቅ ምክንያት ነው። ስለዚህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግዴታ ነገሮችን በመፈፀም፣ ውዳሴና ምህረት መለመንን በማብዛት አላህ ኢማናችንን እንዲያድስልን እንድንለምነው ጠቆሙን።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ፅናት እንዲሰጠንና በቀልባችን ውስጥ ኢማንን እንዲያድስልን አላህን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ኢማን ንግግርም ተግባርም እምነትም ሲሆን በአምልኮ (የአላህን ትዕዛዛት በመፈፀም) ሲጨምር በወንጀል ደግሞ ይቀንሳል።