ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ አንድ አማኝ ባሪያውን የትንሳኤ ቀን እንደሚመሳጠረው እንዲህ በማለት ተናገሩ: የትንሳኤ ቀን አማኝ የሆነ ሰው ወደ ጌታው ይቀርባል። ከርሱ ውጪ አንድም ሰው ምስጢሩን እንዳያውቅበትም ከቆሙ ሰዎች ይከልለዋል። እንዲህም ይለዋል: "እንዲህ እንዲህ ... ወንጀልህን አወቅከው?" እያለ በባሪያውና በጌታው መካከል የሰራውን ወንጀሎች እንዲያረጋግጥ ያደርገዋል። እርሱም "አዎ ጌታዬ" ይላል። አማኙ የደነገጠና የፈራ ጊዜም አላህ ሱብሓነሁ እንዲህ ይለዋል: "ምድር ላይ ላንተ ሸፍኜልሃለሁ። ዛሬ ደግሞ ላንተ እምርሃለሁ።" የመልካም ስራ መጽሐፉም ይሰጠዋል። ከሀዲና ሙናፊቅ ግን በፍጡራን መካከል እየተጠሩ እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹ ናቸው። አዋጅ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን ይባላሉ።