ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን ሞት ጥቁርና ነጭ በሆነ ወንድ በግ ተመስሎ ተይዞ እንደሚመጣ አብራሩ። "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተብሎ ይጠራል። አንገቶቻቸውንና ትከሻዎቻቸውን በመለጠጥ ጭንቅላታቸውንም በማንጠራራት ይመለከታሉ። ለነሱም "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። እነሱም "አዎን ይህ ሞት ነው። ሁሉም አይቶታል ያውቀዋል።" ይላሉ። ከዚያም ተጣሪው "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" በማለት ይለፍፋል። አንገቶቻቸውንና ትከሻዎቻቸውን በመለጠጥ ጭንቅላታቸውንም በማንጠራራት ይመለከታሉ። ለነሱም "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። እነሱም "አዎን ይህ ሞት ነው። ሁሉም አይቶታል።" ይላሉ። ሙክቱ ይታረዳል ከዚያም ተጣሪው፦ "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! እጣፈንታችሁ ያለሞት ዘውትርና ዘላለም መኖር ነው። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! እጣፈንታችሁ ያለሞት ዘውትርና ዘላለም መኖር ነው።" ይላቸዋል። ይህም ለአማኞች ተጨማሪ ፀጋ ለከሀዲያን የቅጣት አለንጋ እንዲሆን ነው። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህን አንቀፅ አነበቡ። {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ እነሱም የማያምኑ ሲኾኑ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የትንሳኤ ቀን በጀነትና እሳት ባለቤቶች መሀል ይፈረዳል። ሁሉም ወደሚዘወትርባት ይገባል። ወንጀለኛ በጎ ባለመሥራቱ ይፀፀታልም ይቆጫልም። መልካም ከመስራት ያጓደለም ባለመጨመሩ ይቆጫል።