ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት የሚያስገቡ ትልልቅ ምክንያቶች ሁለት መሆናቸውን ገለፁ። እነሱም: አላህን መፍራትና መልካም ስነምግባር ናቸው። አላህን መፍራት: በአንተና በአላህ ቅጣት መካከል መጠበቂያ ማድረግህ ነው። ይህም ትእዛዙን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው። መልካም ስነምግባር ደግሞ: ፊትን ፈታ በማድረግ ፣ መልካምን በመለገስና ፍጡራንን ከማወክ በመቆጠብ ነው። እሳት የሚያስገቡት ትልልቅ ምክንያቶች ደግሞ ሁለት ናቸው። እነሱም: ምላስና ብልት ናቸው። ከምላስ ወንጀሎች መካከል:- ውሸት፣ ሀሜት፣ ወሬ ማዋሰድና ሌሎችም ናቸው። ከብልት ወንጀሎች መካከል ደግሞ:- ዝሙት፣ ግብረሰዶምና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።