ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው። (ፍትሃዊ የሚባሉትም) እነዚያ በፍርዳቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና በተሾሙበት ጉዳዮች ላይ ፍትህን የሚያሰፍኑ ናቸው።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

እነዚያ በአመራራቸውና በፍርዳቸው ስር ያሉ ሰዎችን እና በቤተሰቦቻቸው መካከል በፍትህና በእውነት የሚፈርዱ ሰዎች የትንሳኤ ቀን ለነሱ ክብር ይሆን ዘንድ ከፍ ባሉ ከብርሃን በተፈጠሩ ወንበሮች ላይ እንደሚቀመጡ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። እነዚህም ወንበሮች በአርራሕማን ቀኝ በኩል የሚገኙ ናቸው። ጥራት የተገባው አላህ ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የፍትህ ትሩፋቱና በሱ ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
  • ፍትህ በሰዎች መካከል ያሉ ሁሉንም ፍርድና ኃላፊነትን የሚያካትት ጠቅላይ ቃል ነው። በሚስቶች፣ በልጆችና በሌሎችም መካከል ፍትህ ማስፈን ሳይቀር ፍትሃዊነት ውስጥ ይገባል።
  • የትንሳኤ ቀን የፍትሃዊዎች ደረጃ መገለፁን እንረዳለን።
  • ሁሉም በስራው ልክ ስለሚመነዳ የትንሳኤ ቀን የኢማን ባለቤቶች ደረጃ የሚበላለጥ መሆኑን እንረዳለን።
  • በማነሳሳት የማስተማር ዘይቤ የሚማሩትን ሰዎች ትምህርቱን እንዲቀበሉ የሚያነሳሳ ከሆኑት የማስተማር ዘይቤዎች መካከል መሆኑን እንረዳለን።