የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለነቢዩ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ተጠየቀች። እርሷም "በተፈጥሯቸው በንግግራቸውና በተግባራቸው ፀያፍ አልነበሩም፤ ፀያፍን ለመስራትም አይጣጣሩምም አያስቡምም ነበር፤ በገበያ ስፍራ ድምፃቸውን ከፍ የሚያደርጉና የሚጮኹም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ አይመልሱም ነበር፤ ነገር ግን በውስጣቸው ይቅር በማለትና በውጭ ደግሞ በማለፍና ችላ በማለት መጥፎን በጥሩ የሚመልሱ ነበሩ።" ብላ መለሰች።