አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "እኔ ግመሌ ስለጠፋች የሚያደርሰኝን አንድ መጓጓዣ ይስጡኝ!" አላቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እሳቸው የሚሰጡት ምንም ነገር እንደሌለ ነገሩት። እሳቸው ዘንድ የነበረ አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ የሚሰጠውን ሰው እጠቁመዋለሁ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምፅዋት ፈላጊን ለሚመፀውተው አካል በመጠቆሙ ምክንያት ጠቋሚው ከሚመፀውተው ሰው ጋር በአጅር እንደሚጋራ ተናገሩ።